በ2003 ዓ.ም በመጀመሪያ ድግሪ በተሻለ ውጤት ተመርቃችሁ ለረዳት ምሩቅነት ላመለከታችሁ በሙሉ

የዩኒቨርሲቲዎችን የረዳት ምሩቅ የቅጥር ፍላጐት መሠረት በማድረግ ለተመረጣችሁ ዕጩ ረዳት ምሩቃን በዋና ዋና የሀገሪቱ የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ ከነሐሴ 1/2003 ጀምሮ ለ11 ተከታታይ ቀናት ሥልጠና ይሰጣል፡፡ ስለሆነም ለሥልጠና የተመረጣችሁ በሙሉ ሐምሌ 30/2003 ዓ.ም አዳማ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት እንድታደርጉ እያሳሰብን፣ በዕለቱ ሪፖርት በማያደርግ ምሩቅ ፋንታ ከተጠባባቂ ለመተካት የምንገደድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ

  1. ሠልጣኞች የተመረጡት ከዩኒቨርሲቲያቸው በደረሰን የእንግሊዝኛ ቋንቋ መመዘኛ እና በቆይታቸው በነበራቸው የሥነ ምግባር ውጤት “C” እና ከዚያ በላይ ያላቸው ሆኖ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው አጠቃላይ ውጤት (CGPA) መሠረት ነው፡፡
  2. በሥልጠና ጊዜ የሠልጣኞችን የምግብ የመኝታና ለድንገተኛ ህመም የህክምና ወጪን ትምህርት ሚኒስቴር የሚሸፍን ሲሆን፣የትራንስፖርትና ሌሎች የግል ወጪዎች በራሳቸው በሠልጣኞች የሚሸፈኑ ይሆናሉ፡፡
  3. ሥልጠናውን በተሟላ ሁኔታ ያልተሳተፈ በረዳት ምሩቅነት አይመደብም፡፡
Please click here to view the Selected Graduate Assistants list.
If you have a reasonable appeal, please send email to: moe.heducation@yahoo.com.


Message from the Minister, Ato Demeke Mekonnen:
CALL FOR ETHIOPIANS LIVING ABROAD TO COME AND SERVE IN ETHIOPIAN HIGHER EDUCATION INSTITUTIONS

please click here for the document