ለሁሉም የመገናኛ ብዙሃን የቀረበ ጥሪ ባሉበት፣

አውቶሜሽን ተግባራዊ ለማድረግ በተዘጋጀው የምረቃ ዝግጅት ላይ ተገኝታችሁ እንድትዘግቡ ስለመጋበዝ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ ለማዘመን እንዲያስችለው ከአንድ ዓመት ከስምንት ወራት በላይ ሲከናዎን ቆይቷል፡፡ ሶፍትዌሩ በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ፣ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዮት ድጋፍና ትብብር ሲዘጋጅ የቆየ ሲሆን፤ ይህ ከ1 ዓመት ከ8 ወራት በላይ የፈጀው ሶፍትዌር ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ሁሉም ሚዲያዎች እና የሶፍትዌሩ አዘጋጅ ባለሙያዎች በተገኙበት ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ የምረቃ ዝግጅት ለማካሄድ መርሀ ግብር ተይዟለታል፡፡

በእለቱም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ online learning ከተማሪ ቅበላ እስከ ምረቃ ፕሮግራም ድረስ ሙሉ በሙሉ online ሆኖ መማር ማስተማር የሚያስችል መመሪያ ወደ ስራ እንዲገባ ይፋ ይደረጋል፡፡

የምረቃ መርሃ ግብሩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም እና ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዮት ከፍተኛ አመራሮች፣ የኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች፣ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቴክኖሎጂና የሰው ሀብት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና ምክትል፣ የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ፕሬዝደንትና ምክትል እና የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የቦርድ ሰብሳቢና አባላት በተገኙበት ይከናወናል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ ሃምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ አሮጌው ቄራ ወይም ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት ጀርባ በሚገኘው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ግቢ ተገኝታችታችሁ እንድትዘግቡልን በትህትና ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

መድረኩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ ቅድመ-ጥንቃቄዎችን ከግምት በማስገባት የተዘጋጀ ስለሆነ የመግለጫው ወይም የመድረኩ ተሳታፊዎች የተለመዱ የቫይረሱ መከላከያዎችን አሟልታችሁ እንድትገኙ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በዝግጅቱ ላይ መታደም የማችሉ ኢትዮዽያዊያን webinar link:https://zoom.us/)/99869328454 በመጠቀም ቀጥታ መከታተል የምችሉ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡a5gek